ኡስ

Share

ድንገት አይኖችህ ውስጥ አጣሁህ

እንደ እኔ እንደ እኔ እማ 

ሳንናገር ብዙ እንል ነበር

በመሃላችን ግን ሳይባሉ የቀሩት ቃላት ታፍነው ሊሞቱ ሆነ

ከነሱ ተደብቀን እኔ እና አንተ ስንተዋወቅ

እነሱ ታፍነው ሊሞቱ ሆነ

ዛሬ ተናገሩ

ዛሬ አደሙ

ድንገት አይኖችህ ውስጥ አጣሁህ

ድንገት አንደበት ውስጥ ብቅ አልክብኝ

እንደ እኔ እንደ እኔ እማ
  ሳንናገር ብዙ እንል ነበር 

ቀና አልኩና ሁሌ ሚያየኝን ሰማይ አየሁት

ያልተባለው ተባለ

እኔና እኔ ቀረን. . .